Song Lyrics

በልጅነት

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
እኔም እንዲህ እንዲህ ወግ ደረሰኝ ከመቅበዝበዝ እሱ በቃ ሲለኝ ያ መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ በኢየሱሴ ታሪክ ተለወጠ አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን እኔ አውቀዋለሁ አይዞህ ባየለኝ ጌታ እርሱ ባይረዳኝ ማንስ ሊጎበኘኝ ማንስ ሊቀርበኝ በቃ ሲል አበቃ ያ ዘመን አለፈ ጭጋጉ ከፊቴ ይኸው ተገፈፈ ለእኔስ ብዙ ብዙ ብዙ አድርጎልኛል ያደላል ብላችሁ ማን ይቀየመኛል ከናት ካባት በላይ ስለተመቸኝ እንደሱ ያለ የለም ሁሌ እላላሁኝ አዝ፦ ያ መራራ ቀን ያለፈው በእርሱ ነው (2x) ጭጋጉ የተገፈፈው በሱ ነው (2x) ማን ልበለው ምን ልበለው (2x) በምን ቋንቋ በምን አንደበት ይነገራል የእርሱ ደግነት እኔስ ገና ገና በልጅነት አይቻለሁ የጌታዬን ምህረት ሲርበኝም ከእጁ በልቻለሁ ያንን ሁሉ መች እዘነጋለሁ አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ (2x) አይቼዋለሁ የሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (2x) እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ (2x) እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን እኔ አውቀዋለሁ (2x) አዝ፦ ያ መራራ ቀን ያለፈው በእርሱ ነው (2x) ጭጋጉ የተገፈፈው በሱ ነው (2x) ማን ልበለው ምን ልበለው (2x) በምን ቋንቋ በምን አንደበት ይነገራል የእርሱ ደግነት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection