ገና አለኝ ምሥጋና (4x) ገና ገና መቼ ይበቃውና (2x) ገና ገና ዛሬም እንደገና (2x) ገና ገና እሰዋለሁ ገና (2x) ገና አለኝ ምሥጋና (4x) አልጠግብም ባመሰግነው ተመስገን ተመስገን ብለው ኢየሱስ ለእኔ ያረገው ውለታው እጅግ ብዙ ነው አልውልም ሳላነሳሳው ሥሙ እንደሚፈስ ዘይት ነው እንደገና አከብረዋለሁ ምሥጋናዬ እስኪ ይድረሰው አዝ፦ አምጡ ምሥጋና አምጡ (4x) አምጡ ዝማሬ አምጡ (4x) አምጡ ዕልልታ አምጡ (4x) አምጡ ጭብጨባ አምጡ (4x) ጨምሩ ለጌታ ጨምሩ (4x) በተዋበ ዜማ ዘምሩ (4x) ሀያ አራት ሽማግሌዎች ወድቀው ክብርን ይሰጡሀል መላዕክት ቅዱስ ቅዱስ ይገባሀል ለአንተ ይሉሀል እኔም ባለችኝ ጊዜዬ ላክብርህ ውዱ ጌታዬ ምሥጋና ምሥጋና እላለሁ ጌታ ነህ ባለውለታዬ ገና አለኝ ምሥጋና (4x) ገና ገና መቼ ይበቃውና (2x) ገና ገና ዛሬም እንደገና (2x) ገና ገና እሰዋለሁ ገና (2x) አዝ፦ አምጡ ምሥጋና አምጡ (4x) አምጡ ዝማሬ አምጡ (4x) አምጡ ዕልልታ አምጡ (4x) አምጡ ጭብጨባ አምጡ (4x) ጨምሩ ለጌታ ጨምሩ (4x) በተዋበ ዜማ ዘምሩ (4x)