Song Lyrics

ሳሰላስለው

Tekeste Getnet
Negestat Bikeyeru
ምን ልበል ምን ልናገር ቃላትም አጠረኝ የሞትን አዋጅ ሽሮ በሕይወት ኑር ሲለኝ ምህረቱ እንደፀና የሚያውቀኝ ያውቀው የለ ያ ክፉ እንዳይጎዳኝ ቁጣውን ከለከለ እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (2x) እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (2x) እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (2x) እኔማ ሀገር ያውቅ አይደል እኔማ እንደረዳኸኝ (2x) የተጠበቁ ጉድጓዶች ምንጫቸው ነጠፈ (4x) ያም ሄደ እያለፈ ይሄም ሄደ እያለፈ (4x) ብቻውን ህዝቡን የመራ በደረቁ ምድር (4x) ምንኛ ታማኝ ነው ታማኙ እግዚአብሔር (4x) አለኝታዬ (4x) መከታዬ (4x) ቁምነገር ተገኘበት አይጠቅምም የተባለው የሰማይ የምድር ጌታ ከሱ ጋር አብሮ ዋለ በንጉስ ገበታ ላይ ተገኘ በክብር ምስኪኑን የሚያነሳ ማነው እንደ እግዚአብሔር እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (2x) ያለፍኩትን (2x) እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (2x) እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (2x) እኔማ ሀገር ያውቅ የለ/እኔማ እንደረዳኸኝ (2x) ሁሉም ያውቅ የለ (2x) ያሰብኩት እንዳይሞላ እንቅፋት ሲገጥመኝ ከፊቴ እየቀደመ ገለል አረገልኝ ማዕበሉ እንዳያሰጥመኝ ንፋሱን ሲገስፀው አይኔ አይቷል በዘመኔ ፍጥረታት ሲታዘዘው እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (4x) ያለፍኩትን (2x) እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (4x) እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (4x) እኔማ ሀገር ያውቅ የለ እኔማ እንደረዳኸኝ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection