Song Lyrics

እጠብቃለሁ

Tekeste Getnet
Mikinate Bizu New
አዝ:- እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ እጠብቃለሁ ዛሬም እጠብቃለሁ እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ (2x) በለስ እንኳን ባያፈራ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ ወይን ፍሬ ባይጐመራ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ ከብቶች በጋጡት ባይኖሩ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ እርሾች ምግብን ባይሰጡ ዝም ብዬ እጠብቃለሁ አዝ:- እጠብቃለሁ አንተን እጠብቃለሁ እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ እጠብቃለሁ ዛሬም እጠብቃለሁ እጠብቃለሁ ከአንተ የት እሄዳለሁ አንተ አንተ ግን አንተ ነህ አንተ ጊዜ የማይልውጥህ አንተ ዘግይተህ ተነስተህ አንተ ቀድመህ ትደርሳለህ (2x) ያኔ በሸለቆ ደግሞም በተራራ (2x) ወየው ጠፋሁ ብዬ አምላኬን ስጣራ (2x) በጨነቀ ጊዜ ተገልጦ አይቻለሁ ስጋት አይገባኝም ዛሬም አምነዋለሁ ዛሬም አምነዋለሁ (2x) ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (2x) ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (2x) ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (2x) ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (2x) አንገቴን አልደፋም አጋዥ እንደሌለው እንደ ብርቱ ጌታ ኢየሱስ ከኔ ጋር ነው ለምን መቆዘሜ ሃሳቢ እንደሌለው የነአብርሃም አምላክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2x) ይረዳኛል አምናለሁ ይረዳኛል (2x) ያግዘኛል አምናለሁ ያግዘኛል (2x) አንተ አንተ ግን አንተ ነህ አንተ ጊዜ የማይልወጥህ አንተ ዘግይተህ ተነስተህ አንተ ቀድመህ ትደርሳለህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection