Song Lyrics

ክበርልኝ

Tekeste Getnet
Mikinate Bizu New
አዝ፦ ክብርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም ንገሥልኝ ብዬ በልቤ አልረካሁም ከምሥጋና ሌላ ምን አለ የምትወደው ባቀርብልህ ጌታ ምንም ባልሰለቸው ቅዱስ ቅዱስ ብለው ከሚያከብሩህ እኔን ከመደብከኝ ከሚያመሰግኑህ ጥማቴ ይሄ ነው አክብርሀለሁ በቀንም በሌሊትም ምሥጋና እሰዋለሁ :አዝ፦ ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም ሰማይና ምድር ክብርህን ያወራሉ እግዚአብሔር ትልቅ ትልቅ ነው እያሉ እኔም ክብርህን ላውራ ለትውልድ ልናገር የሚመስልህ የለም ወዳጄ ሆይ ክበር :አዝ፦ ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም ፊትህን ወደኔ መልሰሃልና የአንተ ወገን አርገህ ዋጅተኸኛልና ከምርጦችህ ጋራ እኔም ተስማምቸ እስግድልሃለሁ መቅደስህ ገብቸ :አዝ፦ ክበርልን ብዬ ገና አልጠገብኩም የምለው ብዙ አለኝ ስለ አንተ የማወራው አምላኬ ይሔ ነው ብዬ የምናገረው የሚሰማኝና የሚያየኝ ያክብርህ የኔ ብቻ አይበቃም ዘሬም ይገዛልህ ብቻ አንተ ከወደድከው ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection