በለመለመ መስክ እኔን የሚመራኝ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ሁሌ የሚያሰማራኝ ስለ እኔ የሚያስብ ሚጠነቀቅልኝ የማይሰለች ወዳጅ ጌታ ይክበርልኝ አዝ፦ እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም እደገፍሃለሁ እስከዘላለም እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም አታመንሃለሁ እስከዘላለም በትርህ ምርኩዝህ እኔን ያፅናናኛል ከፊቴ ገበታ ተትረፍርፎ ቀርቧል በጠላቶቼ ፊት በዘይት ቀብተህ ታሳርፈኛልህ ፅዋዬን ሞልተህ አዝ፦ እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም እደገፍሃለሁ እስከዘላለም እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም አታመንሃለሁ እስከዘላለም ኢየሱስ እረኛዬ የሚያሳጣኝ የለም እጄን በእጆቹ ይዟል ለዘላለም ስለ ስሙ ብሎ በጽድቅ ይመራኛል በሞት ጥላ ባልፍም እሱ ያሳልፈኛል አዝ፦ እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም እደገፍሃለሁ እስከዘላለም እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም አታመንሃለሁ እስከዘላለም በትርህ ምርኩዝህ እኔን ያፅናናኛል ከፊቴ ገበታ ተትረፍርፎ ቀርቧል በጠላቶቼ ፊት በዘይት ቀብተህ ታሳልፈኛልህ ጽዋዬን ሞልተህ አዝ፦ እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም እደገፍሃለሁ እስከዘላለም እረኛዬ ነህ በምንም አልሰጋም አታመንሃለሁ እስከዘላለም