አዝ፦ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት ላክብርህ እኔ ደጋግሜ ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (2x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x) ተራራው ከፊቴ እንደሰም ቀለጠ (ምሥጋናዬ ነህ) ቃልህም ሲመጣ ጫካው ተገለጠ (ምሥጋናዬ ነህ) እግሮቼም ጸኑልኝ እንደዋላ እግር (ምሥጋናዬ ነህ) ረዳት ሆነኸኛል አምላኬ ክበር (ምሥጋናዬ ነህ) አዝ፦ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት ላክብርህ እኔ ደጋግሜ ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (2x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x) ምህረትህ ከሕይወት በእርግጥም ይበልጣል (ምሥጋናዬ ነህ) ደጅ ጥናት የለም በፍጥነት ያነሳል (ምሥጋናዬ ነህ) ድንጋይ ተደርድሮ ሞት ሲጠብቃት (ምሥጋናዬ ነህ) አፍረቷን ሸፍነህ ሰላም ሂጂ አልካት (ምሥጋናዬ ነህ) አዝ፦ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት ላክብርህ እኔ ደጋግሜ ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (2x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x) ገና ሌሊት ሳለ ንጋት ሳይወጋግን (ምሥጋናዬ ነህ) ምህረትህን ሳስበው ይለኛል አመስግን (ምሥጋናዬ ነህ) ሀሴት አደርጋለሁ በምድር በፊትህ (ምሥጋናዬ ነህ) አንደበቴን ልክፈት ጌታ ላክብርህ (ምሥጋናዬ ነህ) አዝ፦ ልሰዋ የምሥጋናን መስዋዕት ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት ላክብርህ እኔ ደጋግሜ ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (2x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x) አቤቱ ተደንቄያለሁኝና ልሰዋ ምሥጋና (4x)