Song Lyrics

ፍቅርህ ማርኮኛል

Tekeste Getnet
Mikinate Bizu New
አዝ፦ ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (7x) ስላንተ ማውራት አይሰለቸኝም ስምህን ሳነሳ ብውል አልጠግብህም ውበትህን ፍፁም አደንቀዋለሁ መልካምነትህን እተርካለሁ (5x) አዝ፦ ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (7x) ተማርኬያለሁ ስቦኛል ፍቅርህ ከእግርህ ስር ጥሎኛል እንዲገዛልህ ያንተ ምርኮኛ ተረጂ ሆኛለሁ እንደወደድክ አርገኝ ተማርኬያለሁ (5x) አዝ፦ ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል ልቤ ገና ሲያስብህ ሃሴት ያደርጋል እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (7x) በመስቀል ላይ ሆኖ ነፍሱን ለኔ ሰጥቶ ታደገ ጌታዬ በእኔ ፈንታ ሞቶ ከዚህ ሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለው የጌታዬ ኢየሱስ ኧረ ልዩ ነው (5x) አዝ፦ ሥምህ በከንፈሬ ላይ ይጣፍጠኛል ልቤ ገና ሲያስብህ ሀሴት ያደርጋል እውነት ኢየሱስ ጌታ ወድጄሃለሁ ፍቅርህ ማርኮኛል ተማርኬያለሁ (7x) ተማርኬያለሁ (8x) ኧረ ልዩ ነው (8x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection