እኔም እንዲህ እንዲህ ወግ ደረሰኝ ከመቅበዝበዝ እርሱ በቃህ ሲለኝ ያ መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ በኢየሱሴ ታሪክ ተለወጠ አዝ፦ አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (2x) እኔስ ገና ገና በልጅነት አይቻለሁ የጌታዬን ምህረት ሲርበኝም ከእጁ በልቻለሁ ያንን ሁሉ መች እዘነጋለሁ አዝ፦ አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (2x) መቼ ይረሳል ያለፍኩት በሙሉ አማረብኝ ባንተ በኃያሉ ያየኝ ሁሉ እንዲህ ተገረመ ደረቅ በትር ይኸው ለመለመ አዝ፦ አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (2x) አይዞህ ባይለኝ ጌታ እርሱ ባይረዳኝ ማንስ ሊጐበኘኝ ማንስ ሊቀርበኝ በቃ ሲል አበቃ ያ ዘመን አለፈ ጭጋጉ ከፊቴ ይኸው ተገፈፈ ለኔስ ብዙ ብዙ ብዙ አድርጐልኛል ያድናል ብላችሁ ማን ይቀየመኛል ከእናት ከአባት በላይ ስለተመቸኝ እንደእርሱ ያለ የለም ሁሌ እላለሁኝ ሲጠማኝም ውሃ ሲርበኝ ምግቤ ነው በረሃቡ ዘመን ከእጁ በልቻለሁ ማንም በሌለበት በምድረ በዳ ላይ ምንጭን አፈለቀ ከጥሜም አረካኝ የሸሹኝ የራቁኝ የተፀየፉኝ አንቅረው የተፉኝ ጀርባ የሰጡኝ ጌታ ሲጐበኘኝ እርሱ ሲረዳኝ ጐንበስ አሉ ጐንበስ ወዳጅ ሆኑልኝ ሁሉ በርሱ ሆነ ሁሉ በርሱ ሆነ ይህም በርሱ ሆነ ይህም በርሱ ሆነ (2x) አንዳች ከኔ የምለው የለም ሁሉ በርሱ ነው (2x) ያ መራራ ቀን ያለፈው በርሱ ነው በርሱ ነው ጭጋጉ የተገፈፈው በርሱ ነው በርሱ ነው (2x) ማን ልበለው ምን ለበለው (2x) በምን ቋንቋ በምን አንደበት ይነገራል የርሱ ደግነት (2x) አይቼዋለሁ አይቼዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ እኔ አውቀዋለሁ (3x)