ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም ንገሥልኝ ብዬ በልቤ አልረካሁም ከምሥጋና ሌላ ምን አለ ምትወደው ባቀርብልህ ጌታ ከምንም ባልሰለቸሁ (2x) ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሁሌ ከሚያከብሩህ እኔን ከመደብከኝ ከሚያመሰግኑህ ጥማቴ ይሄ ነው እኔ አከብርሃለሁ በቀንም በሌሊት ምሥጋና እሰዋለሁ አዝ፦ ብቻ አንተ ከወደድከው ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (2x) ሰማይና ምድር ክብርን ያወራሉ እግዚአብሔር ትልቅ ነው ትልቅ ነው እያሉ እኔም በተራዬ ለትውልድ ልናገር የሚመስልህ የለም ወዳጄ ሆይ ክበር አዝ፦ ብቻ አንተ ከወደድከው ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (2x) ፊትህን ወደ እኔ መልሰሃልና የአንተ ወገን አርገህ ዋጅተኸኛልና ከምርጦችህ ጋራ እኔም ተስማምቼ እሰግድልሃለሁ መቅደስህ ገብቼ አዝ፦ ብቻ አንተ ከወደድከው ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (2x) የምለው ብዙ አለኝ ስላንተ ማወራው አምላኬ ይሄ ነው ብዬ የምናገረው የሚሰማኝና የሚያየኝ ያክብርህ የእኔ ብቻ አይበቃም ዘሬም ይገዛልህ ክበርልኝ ብዬ ገና አልጠገብኩም ንገሥልኝ ብዬ በልቤ አልረካሁም ከምሥጋና ሌላ ምን አለ ምትወደው ባቀርብልህ ጌታ ከምንም ባልሰለቸሁ (2x) አዝ፦ ብቻ አንተ ከወደድከው ይኸው ምሥጋናዬ ይኸው (4x)