Song Lyrics

ልባርከው

Tekeste Getnet
Mikinate Bizu New
እስኪ ስሙኝ አንዴ ስሙኝ ልንገራችሁ ምስኪኑን ሲያከብር በዓይናችሁ ያያችሁ ኧረ ምን ይባላል ምንስ ይነገራል አምላክ ሥራው ብዙ ይህንን አድርጓል (2x) እስኪ እንደ ጌታ ማን አለ (3x) እንደ እርሱ ያለ ማን አለ (3x) ጌታ ልዩ ነው ልዩ ነው እርሱስ ልዩ ነው ልዩ ነው በእርግጥ ልዩ ነው ልዩ ነው ልዩ ነው እኩያ የለው እንደ አባትም ሆኖ ከአባትም በላይ ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ እንዴት እችላለሁ በቃላት ዘርዝሬ ሥሙን አከብራለሁ ይኸው በዝማሬ አዝ፦ ልባርከው ጌታዬን ልባርከው ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (2x) ሳልሰጋ እኖራለሁ በርሱ ተማምኜ እጅግ በሚመቸው ትከሻው ላይ ሆኜ እኔ አልጨነቅም ምድር ቢነዋወጥ የማመልከው አምላክ ፈፅሞ አይለዋወጥ አዝ፦ ልባርከው ጌታዬን ልባርከው ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (2x) ወጀቡ ቢነሳ ከቶ አያሰጥመኝም ከኢየሱሴ ፍቅር ምንም አይለየኝም የተናገረኝን እንደሚፈፅመው ሁልጊዜ አምነዋለሁ አምላኬ ታማኝ ነው አዝ፦ ልባርከው ጌታዬን ልባርከው ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (2x) የእግዚአብሔርን ክንድ ማን ይከለክላል በብርታትስ በልጦት ማንስ ያቆመዋል ሁሉን እየረታ ሲሰራ የኖረው እንደ ትላንትናው ዛሬም ጌታ ያው ነው አዝ፦ ልባርከው ጌታዬን ልባርከው ልባርከው ኢየሱሴን ልባርከው (2x) እንዳንተ ያለ ማን አለ (3x) እንዳንተ የሚሆን ማን አለ (3x) ጌታ ልዩ ነህ ልዩ ነህ ኢየሱስ ልዩ ነህ ልዩ ነህ አንተስ ልዩ ነህ ልዩ ነህ ልዩ ነህ እኩያ የለህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection