Song Lyrics

ይገርማል

Tekeste Getnet
Mikinate Bizu New
እዚህ እደርሳለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ከቶ በእኔ ጉልበት የሚቻል አይደለም የሚሆን አይደለም እርሱ በፈቃዱ ይህን ካደረገው ከመገረም ውጪ ሰዎች ምን እላለሁ እኔ ምን እላለሁ (2x) አዝ፦ ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል አይደንቃችሁም ወይ ወገኖች በሙሉ ጌታ ያደረገው ለእኔ ለምስኪኑ እርሱ በኔ ሊቀርብ መስዋዕቴን ወዶታል በደረቁ አጥንቴ ዝማሬን ጨምሯል አዝ፦ ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል ያዩኝ ይደነቁ እዚህ በመድረሴ በእርሱ ሆኖልኛል አይደለም በራሴ የማላገኘውን ዘመኔን ብሰራ ጌታ አደረሰኝ እስከ ጺዮን ተራራ ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል ከዘመን ዘመናት ወደዚህ አሻግሮ ቀድሞ እሱ ያየውን ከልጁ ሰውሮ ዛሬ ተገለጠ ፍፃሜው አማረ ስንቱን ጉድ አሰኘ ስንቱ ተገረመ ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል የሚያየኝ ያክብርህ ይደነቅብህ በእኔ በትንሹ ስትሰራ ያየህ ይናገር ክብርህን ምሥጋና ይጨምር ያው ነህ ለዘላለም ወዳጄ ሆይ ክበር ይገርማል አዝ፦ ይገርማል ይገርማል ያረገልኝ ይገርማል ማን ገምቶ ያውቃል ይደንቃል ይደንቃል አሰራሩ ይደንቃል ማን ገምቶ ያውቃል አደንቅሃለሁ አደንቅሃለሁ ያለኝ ይሄ ነው ከተቀበልከው አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ አመልክሃለሁ ያለኝ ይሄ ነው ከተቀበልከው አመልክሃለሁ እወድሃለሁ እወድሃለሁ ቋንቋዬ ይህ ነው ከተቀበልከው እወድሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection