አንደበቴ ከምስጋና በቀር ሌላ አያውቅም ይዘምራል ላንተ ክብር ሰለቸኝ አይልም ደግነትህ በሕይወቴ እጅግ ስለበዛ አሳጣኸኝ ከቶ ምለው ከምሥጋና ሌላ (2x) አዝ፦ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (2x) ከቶ አልሻም በዘመኔ ካንተ ሌላ ለኔ ቆርጫለሁ ላልለይህ ኢየሱስ መድህኔ ብቻ አንተ ክበር እንጂ ይሁን ደስ እንዳለህ አልሰለችም ሁልጊዜ ጌታዬ ባከብርህ (2x) አዝ፦ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (2x) ልማድህ ነው ከፍ ማድረግ ከብረህ የምታከብር ትቢያ አራግፈህ መሸላለም ማብቃት ለቁም ነገር ስንቱ አረፈ እፎይ አለ ወዳንተ ሲጠጋ አመለጠ ባንተ ጉልበት ከጠላት መንጋጋ (2x) አዝ፦ ምክንያቴ ብዙ ነው እጅግ ብዙ ብዙ አጥንቶቼም በርቱ ለአምላኬ ተገዙ ነፍሴ ሆይ አክብሪው ከሞት ያዳነሽን ዝም አትበይ ተነሽ አመስግኝ ጌታሽን (2x) በምስጋና ላይ ምስጋና ገና አበዛለሁ ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (2x) በዝማሬ ላይ ዝማሬ ገና አበዛለሁ ተባረክ ብዬ ሁልጊዜ መቼ እጠግባለሁ (2x)