Song Lyrics

አልተጋነነም

አልተጋነነም የእስካሁኑ የተነገረው በየቀኑ አትጨረስም ተብራርተህ ከተባለልህ በላይ ነህ ትልቅ ከሁሉም ይልቅ ማንንም ደግሞ የማትንቅ አለ በማደሪያው/ በሰማያት አለ ቸርነቱ ያልተጋደለ አማኝ አልሻም ማጋነኛ ታላቅነትህን ለማስረጃ አይቸዋለው በህይወቴ ማእረጌ ሆነህ ገብተህ እቤቴ የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል ስራህ ልዩ ነው ከአይምሮ ያልፋል የጠቢብ ጥበብ ያዋቂው አንተን አይገልጥህ ተራኪው ትልቅ ከሁሉም ይልቅ ማንንም ደግሞ የማትንቅ አለ በማደሪያው/ በሰማያት አለ ቸርነቱ ያልተጋደለ ከሚገርመኝ ከሚደንቀኝ ነገር አንዱ እግዚአብሔር እኔን መውደዱ( 2x) እግዚአብሔር ሶው መውደዱ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection