ውለታውን ያልረሳ ከእኔ ጋር ምስጋናን ያንሳ በጎነቱን ያልረሳ ከእኔ ጋር ምስጋናን ያንሳ ቸርነቱን ያልረሳ ከእኔ ጋር ምስጋናን ያንሳ ያ ለምፃም ፈሪሣዊ ንጉሥን ቤቱ ጠርቶ ፡ በእስራኤል እንዳለልማድ ውሃ እንኳን ማቅረቡን ትቶ ፡ ከሩቅ ሰምታ የመጣችው ፍቅሩ እንደ እብድ ያደረጋት ፡ አብዝታ ክብር ሰጠችው ምንም ነገር ሳይበግራት ፡ ሽቶውን ነሰነሰችው መዓዛውም ቤቱን ሞላ ፡ አበዛች ሲላት አልተወች ቁጭብሎ ሂሳብ የሚያሰላ ፡ ተዋት ብሎ ትዕዛዝ ሰጠ የምታድርገውን ወዶ ፡ ብዙ ይተውለታል ብዙ የወደደ ፈቅዶ ፡ ተዋት እስኪ ተዋት ትዘምርለት ተዋት ፡ እሷ እኮ ናት የምታውቀው ምን እንደ ተደረገላት ፡ እንደገና ወዶናልና ለእርሱ ክብር ይብዛ ምስጋና (X4) ያለፈን የሚያወድስ እሱማ ድንቅ ነው ብሎ ፡ ድንገት ቀኑ ሲከዳ ብያይህም ከሰው ነጥሎ ፡ የዳንክ በተሰቀለው ያነጻህ ደሙ ነውና ፡ በሆነው አትጨናነቅ ያንግዜ ወዶሃልና ፡ ታድያ ሚከስህ ማነው ኑር በሰላም ሳትሰጋ ፡ ድርድር ያለው ይቅረብ አለ ፅኑ ጠበቃ ፡ ያኔ ዓለም ሳይፈጠር ገና ገና ከጥንቱ ፡ ነውር አልባ አድርጎሃል አቁሞሃል በፊቱ ፡ ተውት እስኪ ተውት ይዘምር እስኪ ተውት ፡ እሱ እኮ ነው የሚያውቀው ምን እንደተደረገለት ፡ እንደገና ወዶናልና ለእርሱ ክብር ይብዛ ምስጋና