የነጠፈው ሸለቆምንም ውሃ የሌለበት፡ ስንቱ ጠጥቶት ረካ ተዓምር ሰሪው ሲነኘበት ፡ እሬት ሬት ያለው ህይወት ሲቀምሱት ጣፈጠ ፡ አንተ እጅ ላይ ሲገባ ሁሉም ነገር ተለወጠ ፡ ስደክም እያበረታኝ ሳዝንም እያጽናናኝ ፡(X2) ፡ እግዚአብሔር እኔ አለው እያለ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ ፡ እግዚአብሔር በቂ ነኝ እንዳለ ክረምት በጋ ከእኔ ጋራ ዋለ ፡ መበርቻ መበርቻዬ መበርቻ መበርቻዬ ፡ መበርቻዬ (X3) አንተው ነህ ጌታዬ ፡ መጽናኛዬ ፡(X3) ኢየሱስ ጌታዬ ፡ በራድ አይደል ወይ ትኩስ እንዲሁ ለብ ያለ ፡ ለጌታው መኖር እያቃተው ህይወቱ የሰለለ ፡ የፍቅሩ ጥልቀት እንጂ ፡እስካሁን መሰንበቱ ፡ እንደዝያማ ባይሆን ኖሮ ቁርጥ ነበር መጠፋቱ ፡ ስደክም እያበረታኝ ሳዝንም እያጽናናኝ ፡(X2) ፡ እግዚአብሔር እኔ አለው እያለ ሳይለየኝ ከእኔ ጋራ ዋለ ፡ እግዚአብሔር በቂ ነኝ እንዳለ ክረምት በጋ ከእነ ጋራ ዋለ