Song Lyrics

መባረክ

ያረፈ ሰዉ በጌታ ላይ የተመካ ፡ ከቶ አይሰጋም አያስፈራው ክረምት በጋ አያሰጋ ፡ መቸ ፈራ ልቤ አልደነገጠም ያባቶች አምላክ መች ተለወጠ ፡ ክዳኑ ጽኑ አይታጠፍም እንደልማዴ አልኩኝ እርፍ ፡ በማለዳ በምሽቱ እዘምራለሁ በቸርነቱ ፡ ባንደበተ ሞልቷል ምስጋና በህይወት መኖረ በርሱ ነውና ፡ አላልፈውም ብዬ ደምድሜ ነበረ የሞቱንም አዋጅ ጌታዬ ሰባበረ ፡ ታምር በስቶብኛል የማወራው አለኝ ፡ መባረክ አይደክመውም መዘመር አይደክመኝ ፡ አገር ሰላም ሁሉ ደና ነው ነገሬ ሁሉ በርሱ ነው ያለው ፡ ተዘልዬ በጥበቃው ስር እኖራለው ሳልሸባበር ፡ አላልፈውም ብዬ ደምድሜ ነበረ የሞቱንም አዋጅ ጌታዬ ሰባበረ ፡ ታምር በስቶብኛል የማወራው አለኝ ፡ መባረክ አይደክመውም መዘመር አይደክመኝ ፡
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection