የፍቅር አምላክ የሰላም ባለቤት ቸርነቱን እርሱ ይጨምርበት በሃዘንም ሆነ በደስታ አይለያችሁ ይህ ቸሩ ጌታ (2x) ፍቅር ይሁን በመሃከላችሁ ሰላም ይሁን በመሃከላችሁ ደስታ ይሁን በመሃከላችሁ እረፍት ይሁን በመሃከላችሁ አዝ፦ እንኳን ደስ አላችሁ (4x) ይህንን ውሳኔ በመወሰናችሁ የፍቅር የሰላም ይሁን ጋብቻችሁ እኛ ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ (2x) ፀጋ በረከት ይሙላ በቤታችሁ ሰላም ጤንነት ሁሌ አይለያችሁ ምንም አትጡ ጐዶላችሁ ይሙላ ሁልጊዜ ኑሩ በፍቅር በተድላ (2x) ፍቅር ይሁን በመሃከላችሁ ሰላም ይሁን በመሃከላችሁ ደስታ ይሁን በመሃከላችሁ እረፍት ይሁን በመሃከላችሁ አዝ፦ እንኳን ደስ አላችሁ (4x) ይህንን ውሳኔ በመወሰናችሁ የፍቅር የሰላም ይሁን ጋብቻችሁ እኛ ደስ ብሎናል እንኳን ደስ አላችሁ (2x)