ጐበስ ቀና ብለህ ያኔ በአምሳልህ የፈጠርከው አልተገኘም በስፍራው ሆኖ አንተ እንዳስቀመጥከው በምኞት ተሳበ ወደቀ በጠላት ተረታ እራሱን በራሱ በደለ መቅሰፍትን አመጣ የተስገመገመ . (1) . መድሃኒት ላክለት እንደማይችል አውቅህ እንዲሁ ምህረት አድርግለት አዝ፦ በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው ፍጥረት ተቀሰፈ አለቀ እንዲሁ በከንቱ እሮሮና ሃዘን ያሰማል ሁሉም በየቤቱ ልጆች አዋቂዎች ሳይባል አዛውንቶች ሁሉ ያለአጋዥ ያለጧሪ ቀርተው ጐዳናውን ሁሉ ሞሉ ተንከራታቹን ሰው አስበው ልቡን መልስለት ረሃብ ቸነፈር በሽታውን አንተ አስወግድለት አዝ፦ በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው እረ ይቅር በለን ጩኸታችን ይውጣ የሚያግዝ የለም ወይ እንዲህ ስንቀጣ ወዴት አቤት እንበል ለማን እንንገረው ፍጥረት ተቅበዝብዟል አጋዥ እንደሌለው ከነገሥታት መፍትሄ ጠፍቷል ከጠቢባን ጥበብ ተሰውሯል አቅም ያለው ለውጥን የሚያመጣ አንድም የለም ሚያድነን ከቁጣ አንተ ግን ሁሉን ቻይ ነህና የሚሳንህ ምንም የለምና አግዘው እንጂ ተመልከተው ይሄ ፍጥረት ካለአንተ ማን አለው አዝ፦ በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተቅበዝብዟል በአምሳልህ የፈጠርከው በቃ በለው እስኪ ማረው እንዲህ ተብቀንቅኗል በአምሳልህ የፈጠርከው