Song Lyrics

ገለበጠው እንጂ

Tekeste Getnet
Eweraredalew
ገለበጠው እንጂ ድንገት ጌታ ደርሶ ጠላት ሲጠባበቅ ጉድጓድ ለእኔ ምሶ ነገር ሲፈልገኝ ስፍራ ለማስለቀቅ በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት አዝ፦ ዘምር ዘምር አለኝ ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (2x) እነኛ በፈረሳቸው በሚያልፈው ነገር ታመኑ በሰረጐቻቸው ብዛት እጅጉን ተገዳደሩ ግን እንደዋዛ አለፉ ተሰነቃቅለው ወደቁ የእኔ ግን መተማመኛ አሁንም አለ በክብሩ አዝ፦ ዘምር ዘምር አለኝ ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (2x) በንጉሥ ደጃፍ ተጥዬ ሃማ ግልምጫው በርትቶ ስገድ ሲለኝ አልሰግድም ምንም ቢያይ ተቆጥቶ እጄን አልሰጥም ለጠላት ክፉ ደግ በእኔ ቢያወራ ቀን ቆጥሮ አምላኬ ይመጣል ታሪክን በእኔ ሊሰራ አዝ፦ ዘምር ዘምር አለኝ ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (2x) ጠላት ቢፎክር ቢያቅራራ አዋጅ ቢታወጅ በእኔ ላይ ከቶ እንዳሰበው አይሆንም አምላኬ እኮ አለ በሰማይ አዋጅን በአዋጅ ገልብጦ ጌታ መጣና ቀደመው ነገሩ ተገለበጠ ጠላት ገባ በቆፈረው ገለበጠው እንጂ ድንገት ጌታ ደርሶ ጠላት ሲጠባበቅ ጉድጓድ ለእኔ ምሶ ነገር ሲፈልገኝ ስፍራ ለማስለቀቅ በቆፈረው ጉድጓድ እራሱ ገባበት አዝ፦ ዘምር ዘምር አለኝ ጠላቴን ጥሎ ስላሳየኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection