Song Lyrics

እወድሃለሁ

Tekeste Getnet
Eweraredalew
አዝ፦ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ (2x) (ኦሆ) አንተን አልኩኝ እኔስ (ኦሆ) በጠዋት በማታ (ኦሆ) እረፍት ያገኘሁት (ኦሆ) በአንተ እኮ ነው ጌታ (ኦሆ) አላማህ ገብቶኛል (ኦሆ) የሆንክልኝ ለእኔ (ኦሆ) ዘምሬ አልጨርሰው (ኦሆ) በሕይወት ዘመኔ አዝ፦ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ (2x) (አንተ) የሕይወቴ እረኛ አሃሃ (አንተ) የነፍሴ ጠባቂ ኤሄ (አንተ) ለክፉ ቀን ደራሽ አሃሃ (አንተ) ምስኪኑን ታዳጊ ኤሄሄ (አንተ) የደሃ አደግ አባት አሃሃ (አንተ) ለተጠቃው ፈራጅ አሄሄ (አንተ) እንባ የምታብስ አሃሃ (አንተ) እውነተኛ ወዳጅ አሄሄ አዝ፦ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ (ኦሆ) እወድሃለሁኝ (ኦሆ) ብርጫዬ ነህ ለእኔ (ኦሆ) እንዳንተ አላየሁም (ኦሆ) ኢየሱስ መድህኔ (ኦሆ) ሞቴን ሞተህልኝ (ኦሆ) በሕይወት አኖርከኝ (ኦሆ) የምለው የለኝም (ኦሆ) እወድሃለሁኝ አዝ፦ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ እወድሃለሁ ጌታዬ ጌታዬ ነህ ሁለንተናዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection