የኃያላን ቀስት ተሰባብሮ አለቅነትን ስልጣናትን ሽሮ በግርማው ያለ ሁሉን እየረታ ዛሬም ይገዛል የጌቶች ጌታ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ ጸንቶ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ጐርደድ እያለ ከጠላት ሰፈር ሺ ጦር ቢሰለፍ የማይበገር ድምጹ ነጐድጓድ የሚያስፈራራ ሁሉን የረታ ተራ በተራ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ነጉሰ ነገሥት ግርማዊ ተብለው በምድር ሲኖሩ ክብርን ተጋፍተው ዛሬ ተረስተው አፈር ሆነዋል ሞትን ፈንቅሎ ኢየሱስ ግን ተነስቷል አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ኢየሱስ ጀግና ኢየሱስ ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው መንግሥቱም ጽኑ ነው ማንም አይረታው የተነሱበትን ሁሉንም ገልብጦ ብቻውን ይገዛል እርሱ ብቻ በልጦ አዝ፦ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ ኢየሱስ ጌታ ኢየሱስ (2x)