መቼ ዘነጋሁት የትላንቱን ነገር ከሞት የመትረፌ አያልቅም ቢነገር በአደባባይ ልቁም የአረከውን ላውራ የት እደርስ ነበረ ባልሆን ከአንተ ጋራ (2x) አዝ፦ ትላንትን በአንተ አልፌ ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (2x) ጌታ እንዳንተ ያለ ለእኔ የለም (3x) ጌታ እንዳንተ ያለ ለእኔ የለም (3x) የፀሐዩን ብርታት በጥላ ከልለህ ድቅድቁን ጨለማ በብርሃን ለውጠህ ቁር ሳያገኘኝ እባቡ ሳይነድፈኝ አቤት የእኔ ጌታ ከስንቱ ታደከኝ (2x) አዝ፦ ትላንትን በአንተ አልፌ ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (2x) ትዝ ትዝ ይለኛል ያረክልኝ ሁሉ ሳልቆጥብ ልናገር ዘመኔን በሙሉ ጌታ ማዳንህን ለሰው ሳላወራ አንድም ቀን አያልፍም ስምህን ሳልጠራ (2x) አዝ፦ ትላንትን በአንተ አልፌ ከጨካኙ ከአውሬው ተርፌ ሳልሰጋ ልኑር በደጅህ ለዛሬም ትምክቴ አንተው ነህ (2x)