Song Lyrics

ሲከፋኝ

Tekeste Getnet
Eweraredalew
አዝ፦ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ዘመን ሲከፋ ቀን ሲለዋወጥ አንተ ግን ያው ነህ የማትለወጥ ሁሉን ለይቼ አይቼዋለሁ እንዳንተ ሚሆን የት አገኛለሁ ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (2x) አዝ፦ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ሁሉም እርቆ ጀርባ ሲሰጠኝ ተስፋዬ ያልኩት ድንገት ሲከዳኝ ቀና አደረከኝ እጆቼን ይዘህ ዳግም አቆምከኝ እንዲህ ሸላልመህ ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (2x) አዝ፦ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ቀን የጣለውን እዩት ይሄን ሰው ብለው ሲያወሩ መነሻም የለው ለክፉ ቀን . (1) . መኩሪያ መከታ እያዩኝ ወጣሁ ወደ ከፍታ ሲከፋኝ የማዋይህ ገበናዬን የማሳይህ ለክፉ ቀን ትሆናለህ ቢመኩብህ ታስመካለህ (2x) አዝ፦ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አንስቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ ከአንተ በላይ ለእኔ የለምና ለእኔ አውርቼ አልጠግብህም ኢየሱስ መድህኔ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection