ልጨምር እንጂ እኔም እንዲህ ልበል ሸክሜን ከላዬ ላረክለኝ ገለል ብዙ ብለውሃል ወዳጅ ጓደኞቼ አይበቃም ልጨምር እኔም ተስማምቼ መልካምነትህን ባለኝ አቅም ላውራ ተነግሮ ባያልቅም ጌታ የአንተ ስራ አዝ፦ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ (2x) ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ በላይ በላይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ ከሳሾቼ ቀርበው ሲቀበጣጥሩ በሆነ ባልሆነው ነገር ሲሽርሩ ጉልበት የሚያደክም ልብንም የሚያርድ ነበረ ቃላቸው ቅጥርን የሚንድ ለልጅህ እራርተህ ቁጣህ በተናቸው ፍፁም አልተውከኝም እንደምኞታቸው እነሱ ወደቁ ተሰነካከሉ በአንተ ተደግፌ አመለጥኩ ከሁሉ ቀና አልኩኝ ከአንገቴ የልቤ ደረሰ በየዋሁ ጌታ እምባዬ ታበሰ ያለቀስኩባቸው እነኛ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ በጌታዬ ብርታት ቀና አደረገኝ ቀና የልቤ ደረሰ በየዋሁ ጌታ እምባዬ ታበሰ ያለቀስኩባቸው እነኛ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ በጌታዬ ብርታት አዝ፦ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ (2x) ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ በላይ በላይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ አትገመትም እንደዚህ ተብለህ በሰው አይምሮ መቼ ተመዝነህ መልካምነትህ ፍቅርህም ቢወራ ተነግሮ አያልቅም ሁሉም በየተራ እልፍ ልሳኖች ሺህ ቃል ቢደረደር ሊገልጥ አይችልም ጌታ የአንተን ፍቅር አዝ፦ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ (2x) ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ በላይ በላይ መልካም ነህ ከተባልከው በላይ ስትሰራ የሌለብህ ከልካይ የእኔ ጌታ ሁልጊዜ ኤልሻዳይ ቀና አልኩኝ ከአንገቴ የልቤ ደረሰ በየዋሁ ጌታ እምባዬ ታበሰ ያለቀስኩባቸው እነኛ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ በጌታዬ ብርታት ቀና አደረገኝ ቀና የልቤ ደረሰ በየዋሁ ጌታ እምባዬ ታበሰ ያለቀስኩባቸው እነኛ ዘመናት አልፌያቸዋለሁ በጌታዬ ብርታት