Song Lyrics

ማን ያንከባለው

ማን ያንከባለው ይህን ድንጋይ ብዬ ስማትር ታች ላይ ቀና ብዬ እንዳይ አደረከኝ ለካስ ተንከባሏል ያስጨነቀኝ ( 2x) አሻቅቦ ማየት ከሁኔታ በላይ አድርጎኛል ጌታ ችግርን እንዳላይ ሻገር ሻገር ብሎ አይኔ ከሩቅ አይቶ ያመሰግንሃል ሁሉን በአንተ ረስቶ ( 2x) ይኸው (፬x) ጌታ ተቀበለው ምሥጋናዬ ይኸው ጌታ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው ( 2x) ጭንቅ ጥብብ ወየው ያልኩበት አንገት ያስደፋኝ ያለቀስኩበት ያኔ ያስፈራራኝ ልቤን ያራደው ተንከባለለ ከፊቴ ያለው ( 2x) አሻቅቦ ማየት ከሁኔታ በላይ አድርጎኛል ጌታ ችግርን እንዳላይ ሻገር ሻገር ብሎ ዓይኔ ከሩቅ አይቶ ያመሰግንሃል ሁሉን በአንተ ረስቶ ( 2x) ይኸው (፬x) ጌታ ተቀበለው ምሥጋናዬ ይኸው ጌታ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው ( 2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection