እንዲህ ያለ መውደድ ከቃላት ያለፈ ስለጠላቶቹ ነፍሱን ያሳለፈ ፍጥረት በሙሉ ተደንቆ ዋለ ፍቅር እንዳንተ የለም እያለ ፀሐይም አለች ብርሃን ለምኔ መስቀል ላይ ሲውል ደጉ መድህኔ አዝ፦ ባህሪህ ባህሪህ ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ ባህሪህ ባህሪህ ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ ወደ ሙት ሲነዳ (ደግ ነህ) የአዳም ዘር በሙሉ (ደግ ነህ) ሞቱን ሞተህለት (ደግ ነህ) ደርሰህ ካለህ ሁሉ (ደግ ነህ) ነፍስን እስከመስጠት (ደግ ነህ) ፍቅርህ ተፈትኖ (ደግ ነህ) ከፍርድ አመለጠ (ደግ ነህ) ሁሉ በአንተ ሆኖ (ደግ ነህ) አዝ፦ ባህሪህ ባህሪህ ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ ባህሪህ ባህሪህ ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ ለፃድቅ የሚሞት በጭንቅ ከተገኘ ሃጥእ ተስፋ ቆርጦ መኖር ባልተመኘ ግን ተገለጠ ፍቅር ለሁሉ አመለጡብህ ጌታን እያሉ ለየት ያለ ነው ያንተስ ፍቅር መሰከሩልህ ሰማይ ምድር ፡ አዝ፦ ባህሪህ ባህሪህ ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ ባህሪህ ባህሪህ ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ አቅም አጥተህ አይደል ተሸንፈህ በጨካኞች ጡንቻ ላይ መውደቅህ እንደሚታረድ በግ እየነዱ በመስቀል ሊገሉህ ወደዱ ( 2x) አዝ፦ ባህሪህ ባህሪህ ቢደንቃቸው ደግ ነህ አሉህ ባህሪህ ባህሪህ ቢያስገርመኝ ደግ ነህ አልኩህ አወይ አጨካከን ጠፍቶ የሚራራ እያወካከቡ ነዱት በተራራ አፉ አልተከፈተ ክፉ አልተናገረ ጭራሽ ለሚጠሉት ይማልድ ጀመረ ወዶ አለም ቢያወድሰው በእርግጥ ስለሚገባው ነው ለእኛ ብሎ ታርዷል እና ለእርሱ ይገባል ምስጋና ( 2x)