አዝ፦ ልቤ ፀና ልቤ በአንተ ፀና ( 2x) ቃልህን ይዣለሁ ባይታይ ደመና ዘምር ዘምር አለኝ ልቤ በአንተ ፀና አዝ፦ ልቤ ፀና ልቤ በአንተ ፀና ( 2x) ሳይቀየር ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሲያመሰግን በአምላኩ ተማምኖ ምድረበዳን የሚያለመልመው በረሃውን ገነት አደረገው ሳይቀየር ሁሉ እንዳለ ሆኖ ሲያመሰግን በአምላኩ ተማምኖ ምድረበዳን የሚያለመልመው ድንገት ደርሶ ታሪኩን ቀየረው በገናዬ ከተሰቀለበት ይውረድና ቅኔን ልቀኝበት ሁኔታው ሳይቀያየር አውቅበት የለ ለአንተ መዘምር ምሥጋና ለሥምህ ምሥጋና ለክብርህ ይገባሃል ጌታ አይጓደለብህ ዝማሬ ለሥምህ ዝማሬ ለክብርህ ይገባሃል አንተስ አይጓደለብህ ባያድነን እኛስ ለአንተ አንሰግድም ላቆመውከው ምስል ፈፅሞ እጅ አንሰጥም ሰባት እጥፍ ቢነድም እሳቱ ይመለካል የእኛስ ክንደ ብርቱ ( 2x) ባሪያዎችህ ወህኒ ቤት ተጥለው ግን ሲያመልኩ ቅዱስ ቅዱስ ብለው የወህኒውን መሠረት አናውጠህ ተገልጠሃል እስራት በጣጥሰህ ቅዱስ (፫x) ጌታ ኢየሱስ ኃያል (፫x) የሚመስልህ ታጥቷል ( 2x)