Song Lyrics

ይታወቅልኝ

Yitawekilign

በሰፊው ጎዳና ትውልድ ሲተራመስ የልቡ ላይሞላ ያሰበበት ላይደርስ በቅጭኑ መንገድ ጌታ ብቻ ይዞ ወደ እረፍት ይገባል ተጉዞ ተጉዞ/2 በሰፊው ጎዳና ትውልድ ሲተራመስ የልቡ ላይሞላ ያሰበበት ላይደርስ በቅጭኑ መንገድ ጌታ ብቻ ይዞ ከፂዪን ይደርሳል ይገባል ተጉዞ ተጉዞ/2 ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የእርሱ ነኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ ምርጫዬ ጌታ ነው እኔስ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ የሞት መውጊያ አያሰጋኝ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ ሲዖል ገሃነብ አያስፈራኝ ግርግር ቢበዛ ግፊያ በመንገዱ ጠቢባን ነን ባዮች ወደዚያ ቢነጉዱ የምህረቱ ደጃፍ ድንገት ሳይዘጋ እየሱስን ብሎ ማምለጥ አለው ዋጋ/2 ግርግር ቢበዛ ግፊያ በመንገዱ ጠቢባን ነን ባዮች ወደዚያ ቢነጉዱ የምህረቱ ደጃፍ ድንገት ሳይዘጋ እየሱስን ይዞ ማምለጥ አለው ዋጋ/2 ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ ምርጫዬ ጌታ ነው እኔም የእርሱ ነኝ ይታወቅልኝ ይታወቅልኝ ምርጫዬ ጌታ ነው እኔስ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ የሞት መውጊያ አያሰጋኝ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ ሲዖል ገሃነብ አያስፈራኝ እድል ፋንታዬ እግዚአብሔር ነው የኔ ጠበቃ እየሱስ ነው እድል ፋንታዬ እግዚአብሔር ነው የኔ አማላጅ እየሱስ ነው የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ የሞት መውጊያ አያሰጋኝ የእርሱ ነኝ የእርሱ ነኝ ሲዖል ገሃነብ አያስፈራኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection