Song Lyrics

አጠገቤ ነህ

Ategebe Neh

አልበር እንደ ንስር ከደመናው በላይ ወዴት ነው መገኛህ ስፍራ ወሰን አለው ወይ በወርድ ቆላ ብወጣ ወደ ደጋ ውስጥ ውስጤን ታወቀኝ ጌታ አለ ከኔጋ አጠገቤ ነህ ጌታ አጠገቤ ዘልቀህ ገብተሃል ከውስጥ ከልቤ ይታወቀኛል ሁሌ አብሮነትህ ሰላም ተሰማኝ በመገኘትህ ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ ሁሉ ደህና ነው ሁሉ በጎ ነው ጌታ ካለ ሁሉ ሸጋ ነው ውስጤን ስሰማው ሳደምጠው ሁሉ ሰላም ሰላም ነው ውጪውን አይቶ ልቤ እንዳሰጋ እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ እሩቅ አይደለህም ካለሁበት አለህ እስከ ምድር ጫፍ ብሄድ በዛም ትገኛለህ ፍጥረት ባንተ አብሮ የለህም ብትባል ምስክር አልሻም ስራህ ይናገራል አጠገቤ ነህ ጌታ አጠገቤ ዘልቀህ ገብተሃል ከውስጥ ከልቤ ይታወቀኛል ሁሌ አብሮነትህ ሰላም ተሰማኝ በመገኘትህ ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ ሁሉ ደህና ነው ሁሉ ሰላም ነው ጌታ ካለ ሁሉ ደህና ነው ውስጤን ስሰማ ሳደምጠው ሁሉ ሰላም ሰላም ነው ውጪውን አይቶ ልቤ እንዳሰጋ እርፍ አለ ባንተ ተረጋጋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection