Song Lyrics

በል ደህና ውጣ

Bel Dehna Wita

በል ደህና ውጣ በል ደህና ግባ ተብያለሁኝ ልቤ እንዳይሰጋ/2 ምንም አይቆምም ከፊት ለፊቴ ተረክቦኛል እጁ ላይ ነው ቤቴ/9 ኮራ በል እንጂ ዛሬም ኮራ በል ቀና ብለህ ሂድ ደፋ ደፋ አትበል ኑር ሰላም ብሎ ዘላለሜን ያዘው ክብር ይሁንለት ልቤን ላሳረፈው ቅጥር ቀጠረልኝ ጠላቴ ማይደፍረው/2 ታዲያ ምን አሰጋኝ ዚሪያዬን ቢዞረው የምታመንበት ጌታ ከኔ ጋር ነው ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው አይዞህ ብሎኛል ሁሉን ቻዩ አባቴ ተደላደልኩኝ ፀናልኝ ጉልበቴ ያለማቋረጥ ጠላቴ ቢዞረኝ ጌታዬን ይዤ ኧረ ምን አሰጋኝ ቅጥር ቀጠረልኝ ጠላቴ ማይደፍረው/2 ታዲያ ምን አሰጋኝ ዚሪያዬን ቢዞረው የምታመንበት ጌታ ከኔ ጋር ነው ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው ከኔ ጋር ነው ጌታ ከኔ ጋር ነው ይረፍ እንዲ ልቤን ምን አሰጋው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection