Song Lyrics

በተዘጋ ቤት ውስጥ

Betezega Bet Wist

በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል ሰላም ይሁን ለኔ ብለሃል ችግሬን የረሳሁብህ ልነሳ እስቲ ያምልክህ በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል ሰላምህን ለኔ ሰተሃል ችግሬን የረሳሁብህ ልነሳ እስቲ ያምልክህ ኮቴ ሳይሰማ በር ሳይንኳኳ ከቤቴ የገባህ ጌታ አንተ ነህ ለካ የታለ ያ እጅህ ስለኔ የደማው ቁስልህ የሻረበት መገኛዬ እርሱ ነህው በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል ሰላም ይሁን ለኔ ብለሃል ችግሬን የረሳሁብህ ልነሳ እስቲ ያምልክህ በተዘጋ ቤት ውስጥ ገብተሃል ሰላምህን ለኔ ሰተሃል ችግሬን የረሳሁብህ ልነሳ እስቲ ያምልክህ በር ዘግተን አዝነን ተቀምጠን እንዳይገድሉን አይሁዶችን ፈርተን ውሎ አደረ ልብ እንደዋለለ ምጠብቀው ጌታ ወዴት አለ ከመከራው የሚያድን ሲታጣ ሲጨላልም ቀን እስከሚወጣ ከተፍ ሲል ባልጠበቅነው ሰዓት ተወገደ መጨነቅ ማባባት የሰላሜ ምንጭ አንተ ሰላሜ ሆይ ላፍታ አትለየን ባክህ ከቤተ ቆይ ጌታ መገኘትህን አትውሰድብኝ ጥጋቤ አንተው ነህ ሌላ ሁሉ ይቅርብኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection