Song Lyrics

አማን አይደለም ወይ

Aman Aydelem Wey

ይህንን ተግዳሮት ለሚያርቅለት ንጉስ ቃሉን ሰጠ ልጁን ሊድርለት ግብር እንዳይከፍል ይሁን ባለፀጋ እጅ መንሻ ይኸው ደፍሮ ለሚዋጋ ሽልማቱም ይቅር ከሱ የለም ልቤ አምላኬ እንዲገለጥ ነው የኔ ሃሳቤ እጅ መንሻው ይቅር ከሱ የለም ልቤ አምላክ አለ ይባል ይሄ ነው ሃሳቤ አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ ሆ ብሎ ወጣ እንደቀደመው ደሞ መዋጋት እስራኤል ልምድ አለው ይዛሬው ውጊያ አንድ ለአንድ ማነው ሚገጥመኝ ብሎ ሲንጎራደድ ደግሞ ፎከረ ጎልያድ በያደባባዩ ታላላቆችን ጭጭ አሉ አይተው እንዳለዩ ግን ምድረበዳ በግሉ አምላኩን ያወቀ እገጥማለሁኝ ብሎ ወገቡን ታጠቀ አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ እንደልማዱ ከሰልፉ መሃል ቆሞ ሲናገር ልብን ያቀልጣል ከእስራኤል ወገን ጠፍቶ ሚገጥመው ሲረበሽ ዋለ አቤት ስንቱ ሰው ደግሞ ፎከረ ጎልያድ በያደባባዩ ታላላቆችን ጭጭ አሉ አይተው እንዳለዩ ግን ምድረበዳ በግሉ አምላኩን ያወቀ እገጥማለሁኝ ብሎ ወገቡን ታጠቀ አማን አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የወገኔ ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ ሰላም አይደለም ወይ ከተማው መንደሩ የእስራኤል ልጆች ምነው ተሸበሩ ይሄ ያልተገረዘ ከሆነ ሚያስጨንቅ ባምላክ ስም ልግጠመው ማንም ልቡ አይውደቅ አምልካክ አለኝ ሚዋጋልኝ ካንበሳ ከድብ ያስመለጠኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection