Song Lyrics

ሰው ከንቱ

Sew Kentu

ባጎረሰ የተነከሰ በቤቱ አለ ስንቱ እያለቀሰ ለክፉ ቀን ነበረ ወዳጁ ግን ተገኘ ሲሸምት እደጁ ከገበታው ላይ የበላ ተረከዙን ደግሞ ቢያነሳ ለትምህርት ተፅፏል በቃሉ ገሮች ሆይ ይህንን ልብ በሉ ሳዖል አስተካክሎ ስል ጦሩን ወረወረ ሊገል ዳዊትን አምላክ አተረፈው ገብቶ ጣልቃ የወንድምም ክፉ አለ ለካ ይቅር አይወራ ክፉም አትናገር ልመድልኝ ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር ጉድጓዱን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት ግዜ እስኪያስተምረው አንተ አትፍረድበት ይሁን አይወራ ክፉን አትናገር ልቤ አስተውል ልቤ ሁሉን ችሎ ማደር ጉድጓዱን የሚምስ ራሱ ሊወድቅበት ግዜ አለው ለሁሉ ተው አትፍረድበት ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ተረዳው ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ገብቶኛል ሰው ከንቱ ቢጠበብ ከንቱ ከንቱ ከንቱ ቢያስተውል ከንቱ ከንቱ ከንቱ ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ መሰዋቱን ጌታ ችላ ቢለው ተቆጥቶ ወንድሙን ገደለው ያድርግ እንጂ እርሱ እንደወደደ አንዱን ትቶ አንዱን ከመወደደ ወንድምህን ወዴት አረከው እንዳላየ ሆኖ ቢጠይቀው አይደለሁም የሱ ጠባቂ ብሎ መለሰ ያ አላዋቂ ደሙ ጮክ ብሎ አወራ ያለበደል ምነው ግፍ ተሰራ ተንከራታች ሆነ በምድር ላይ እግዚአብሔር አይቷል ሰው ባያይ ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ተረዳው ሰው ከንቱ ሰው ከንቱ/3 መሆኑን ገብቶኛል ሰው ከንቱ ቢያገኝም ከንቱ ከንቱ ከንቱ ባያገኝ ከንቱ ከንቱ ከንቱ ጌታ ካልረዳው ከንቱ ከንቱ ልቡን ካልያዘው ከንቱ ከንቱ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection