Song Lyrics

ጎዳና ላይ

Godana Lay

ምልክት አለብኝ አንተ እንደረዳኸኝ ተጥሎ የኖረ ያቁስለኛ እኔ ነኝ ምልክት አለብኝ በሰውነቴ ላይ ሁሉን የረሳሁት ጌታ ባንተ አይደል ወይ/2 ባንተ ነው ነው ጌታ ባንተ ነው ቁስለኛው ተነስቶ ሰው የሆነው ባንተ እኮ ነው ነው ጌታ ባንተ ነው ምስኪኑ ተነስቶ ሰው የሆነው ጎዳና ላይ ጎዳና ላይ እንዳላየ ሆኖ ስንቱ አልፎኝ የለ ወይ ለየት ይላል ዛሬስ የገጠመኝ ሰው ቢርቅ እኔ አለው አለኝ ይሄማ ይወራ ይህማ ይነገር አንተ ባትደርስልኝ ምን ይወጠኝ ነብር/2 ይሄማ ይወራ ይህማ ይነገር ጌታ ባትደርስልኝ ምን ይወጠኝ ነብር/2 ኧረ እንዴት እሆን ነበር ያገዘኝ ጌታዬ ይክበር እኮ እንዴት እሆን ነበር የረዳኝ ጌታዬ ይክበር እስቲ እንዴት እሆን ነበር ያገዘኝ ጌታዬ ይክበር ያልጠገረ ተስፋው ተሟጦ በቤተ መቅደስ ደጅ ተቀምጦ ከሚወጣና ከሚገባው ሰው እየለመነ ፊት የገረፈው እኔው ነኝ ያ ሰው ድንገት ተነስቶ ከመቅደስ ገባ የሚያየው ሁሉ ግራ እስኪጋባ አመሰገነ ባደባባይ ምን ነካው የሚል ማነውስ ከልካይ/2 ተመስገን ይላል ከፍ በል ይላል እርሱም እንደሰው ወግ ማረግ አይቷል/2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection