ክብሬ ጌጤ አንተ ነህ ለእኔ ሽልማቴ አጠገቤ ሳይህ ወደድኩህ አባቴ ደጅ አላስጠናኸኝ አንተን ለማግኘት ሳልፈልግህ መጥተህ ገባህ ከእኔ ቤት አዝ፦ አንተን ተስፋ አድርጌ ጌታን ተማምኜ ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (2x) ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (4x) የጠበኩት ሁሉ ያሰብኩት ባይሞላ አንተ ካለህልኝ ምነው ባይበላ ተስፋዬ አንተ ነህ የሙጥኝ እላለሁ ከአንተ ጋራ ኖሮ ሞት ለእኔ ክብር ነው ትምክቴ ነህ በአንተ እታመናለሁ የትናንቱን እንዴት ረሳዋለሁ ተንከባክበህ አሳድገኸኛል ለነገዬ ምንስ ያስፈራኛል (2x) ዓለም ሁሉ ክዶህ ብቻዬን ብቀር እኔስ አለኝ ለእኔ ሕያው ምስክር የልጅነቴ አምላክ ከእኔ ጋር ሆነሃል ጐጆዬ ስትገባ ሙሉ ዓይኔ አይቶሃል አዝ፦ አንተን ተስፋ አድርጌ ጌታን ተማምኜ ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (2x) ኧረ እኔስ ምን አጥቼ (4x) የአጀበ ሲበተን ጐኔ የነበረው ጊዜና ሁኔታ ወረት ሲቀይረው አንዱ እንደ ሺህ ሆነ ቤቴን አድምቀሃል የጐደለኝ የለም ወዳጄ ሆነሃል