Song Lyrics

ያላየሁት ዓለም

Mesfin Gutu
Zare lay Kome
የተደረገልኝን አይቼ ከአንተ የተቀበልኩትን አይቼ በፊትህ ቅኔን ተቀኘሁኝ እንዲህ አልኩኝ አንተ ጌታዬ ነህ አንተ ኧረ አንተ ንጉሤ ነህ አንተ አንተ ጌታዬ ነህ አንተ ኧረ አንተ አባቴ ነህ አንተ ያላየሁት ዓለም ያልቀመስኩት ኑሮ በጌታ ሆነልኝ ይገርማል ዘንድሮ ተመስገን ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል የአምላኬ ቅናት ይህንን አድርጓል ተመስገን ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል የአምላኬ ቅናት ይህንን አድርጓል (2x) እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ (እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ) (2x) ደግሜ ደግሜ ጌታን አመልካለሁ ጌታን አከብራለሁ (2x) እርሱ የእኔ አባት መድሃኒቴ ነው (3x) አቅም ብርቱ ሳለ ጉልበቴ ሳይደክም ለዚህ ከንቱ ዓለም ልቤን አላዝልም አቅም ብርቱ ሳለ ጉልበቴ ሳይደክም ለዚህ ከንቱ ዓለም ልቤን አላዝልም (2x) እንደምን ይቻላል ያለ ጌታ ሆኖ በራስ መተማመን ድጋፍ ተሸፍኖ ዓለምን ናቅ አድርጐ ጌታን መወዳጀት ይህ ታላቅ ጥበብ ነው የሠማይ በረከት ዓለምን ናቅ አድርጐ ጌታን መወዳጀት ይህ ታላቅ ጥበብ ነው የሠማይ በረከት (2x) እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ (እንዲህ ነው ጌታ ሲረዳ እንዲህ ነው ኢየሱስ ሲያሳርፍ) (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection