እኔን የሚገርመኝ እግዚአብሔር ነው የፍቅሩ ብዛት እንዴት ድንቅ ነው (2x) የከበረ ነገር ከእርሱ ይፈልቃል ተስፋ ያጣውን ሰው ሞገስ ያገኘዋል ምስኪን ምጻተኛ አሃ አሃ አቅም ያነሰዉ የኢየሱስ ደግነት አሃ አሃ ሰላም ወረሰዉ አዝ፦ ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ነገሬን ቀየረው ቀያየረው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ህመሜን ከላዬ በፍቅሩ አከመው የደከመ ሕይወቴን በቃሉ ፈወሰው ፈጥኖ ተመለሰ የነፍሴ እርካታ/ደስታ እስኪ ለጌታዬ ልቅረብ/አምጡልኝ በምሥጋና (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ነገሬን ቀየረው ቀያየረው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ዓይኖቼ ሲቀኑ ጌታ ወዳለበት ጠል ከላይ ወረደ አባቴ ካለበት በትዝታ መኖር አሃ አሃ ጠፋ ከሕይወቴ ፈጥኖ ሲሆንልኝ አሃ አሃ ሠማይ እረዳቴ አዝ፦ ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ነገሬን ቀየረው ቀያየረው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ኢየሱስ ቤቴ ገባ (2x) አባ ቤቴ ገባ ሕይወቴን ለወጠው ለዋወጠው ምህረቱ በዝቶ ኦ ባረከው (2x) ብቻዬን ትቶኝ አልሄደም ጌታዬ ጌታዬ ለብቻዬ ትቶኝ አልሄደም ወዳጄ ወዳጄ ለአንድ አፍታ ትቶኝ አልሄደም ጌታዬ ጌታዬ ብቻዬን ትቶኝ አልሄደም ወዳጄ ወዳጄ (2x) ጌታዬ ባለውለታዬ (7x) አንተ ብቻ . (1) .