ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ ዞር በል የሚልልኝ አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (2x) ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (2x) ከእናት ካባቴም በላይ ለኔ ራርተህ ስላየሁ (አሃሃ አሃ) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም እላለሁ ስደክም አበርትተህ ራሴን በዘይት ቀባህ (አሃሃ አሃ) ጽዋዬም ተረፈልኝ ኢየሱስ ክብርህ ይስፋ ጌታ ክብርህ ይስፋ ውዴ ክብርህ ይስፋ (2x) ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል (ሰው ቢጥል) ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል ከብሮ ያከብራል ከፍ ያደርጋል ሰው ቢጥል እግዚአብሔር ያነሳል (ሰው ቢጥል) (2x) እንቅልፍ እንደያዘው እንደተኛ ሰው (2x) መስሎኝ ነበር እኔስ ግድ ማይለው (2x) ኧረ ይሄስ ሰው ሃይለኛ ነው ተነሳና ዞር በል አለው ኧረ ይሄስ ሰው ሃይለኛ ነው ተነሳና ጸጥ በል አለው አዝ፦ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ ዞር በል የሚልልኝ አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (2x) ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (2x) የምስኪን ወዳጅ ሆነህ በጐጆዬ ውስጥ ገባህ (አሃሃ አሃ) የዘመመው ቤቴ ይኸው ባንተ ቀና ታዲያ ልዘምር እንጂ ለምን ላጉረምርም (አሃሃ አሃ) በጐጆዬ ውስጥ ያለው ኢየሱስ ይክበር ውድዬ ይክበር ጌትዬ ይክበር ወድዬ ይክበር አዝ፦ማዕበሉን በስልጣን የሚገስጽልኝ ዞር በል የሚልልኝ አባት አለኝ እኔ አባት አለኝ (2x) ረዳት አለኝ እኔ ረዳት አለኝ (2x)