Song Lyrics

አንተ የእኔ

Mesfin Gutu
Teshager Yalew
አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (2x) ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (2x) ማን ኧረ ማን ማን ይወስድብኛል አንተን ከኔ (2x) ተማመለህ እኮ ነው የኔ ጌታ በጭንቅ የወለድከኝ በጎልጎታ እድሜዬን በሙሉ ሰጥሃለሁ ዘላለም ለቃልህ እገዛለሁ እገዛለሁ ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ ታዲያ ታዲያ (2x) እንደመሸ አይቀርም ለሊቱ ይነጋል (4x) ማንጋት ልማድህ ነውና ማንሳት ልማድህ ነወና ማክበር ልማድህ ነወና ማስዋብ ልማድህ ነውና ውዴ የኔ ነው እኔም ደግሞ የእርሱ ነኝ የየሱስ ነኝ (2x) ማንም አይገባም በመሀላችን ጉድለት የሌለበት ነው ፍቅራችን ጊዜም ሁኔታም አይሽረዉም ለኔስ ኢየሱሴ ልዩ ነዉ ልዩ ነዉ ታዲያ ልዘምር እንጂ ልቀኝ እንጂ ለባለውለታዬ ልኑር እንጂ አሃሃሃ ታዲያ ታዲያ (2x) አንተ የኔ የራሴ የግሌ የኔ ባስጨናቂው ለት ለኔ ደርሰህ በጨለማ እኔ ላይ ብርሃን ይብራ ብለህ ታሪኬን ለውጠህ ታዲያ ልበልህ እንጂ አንተ የኔ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection