Song Lyrics

ውበትህ ከሰው ልጆች

Mesfin Gutu
Teshager Yalew
ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (4x) ካጠገቤ ቆመህ አበርትተኛል ከወዳጅም ወዳጅ ወዳጅ ወዳጅ ሆነኸኛል መደገፍ አንተን ነው መታመን ባንተ እንጂ ሁሉን እየረታህ ሆንክልኝ ሞገስ ሆንክልኝ ሞገስ (2x) ሆንክልኝ ብቃት (2x) ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (4x) ካቻምናን አለፍኩኝ ባንተ በመደገፍ ዘንድሮን አልሰጋም ስለሆንከኝ ሞገስ ደስታ የኔ ነው ለቅሶ ለጠላቴ ይሄንን ያረገው ከፍ ይበል አባቴ ከፍ ይበል አባቴ (4x) ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (4x) ማንንስ እረስተህ ማን ጥለህ ታውቃለህ ይልቁን ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ ታደርጋለህ ደካማው በረታ ቆመ በእግሮቹ ታሪክ ተለወጠ እያየ ጠላቱ እያየ ጠላቱ (4x) ውበትህ ከሰው ልጆች ሁሉ ይበልጣል ኢየሱሴ እንተን ማን ይመስልሃል ሲወራ ሲነገር ሲተረክ ቢዋል እንደ ኢየሱስ ያለ የት ይገኛል እንዳባቴ ያለ የት ይገኛል (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection