Song Lyrics

ታለፈ ያ ዘመን

Mesfin Gutu
Talefe Ya Zemen
እንዴት አልፈዋለሁ ያልኩትን ያንን ቀን ክንድህ አሻገረኝ አለፍኩት ያንን ቀን ዛሬስ ተረዳሁኝ ቆምኩኝ እንደገና ቀና አልኩኝ ከአንገቴ ታለፈ ያ ዘመን ታለፈ ያ ዘመን (4x) (በኢየሱስ የማይታለፍ ምን አለ) ታለፈ ያ ዘመን (4x) ምንም ሳልናገር ቃል ሳይወጣ ከአፌ ሁሉን መለሰና ሆነልኝ ድጋፌ ያ ሁሉ ጥያቄ ኧረ ወዴት ገባ ማንስ አበሰልኝ የዓይኖቼን እንባ እንደ እናትም ሆነ ከእናትም በላይ ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ እንደ አባትም ሆነ ከአባትም በላይ ብዙ አድርጐልኛል ኢየሱስ ኤልሻዳይ (2x) መግለጥ አቅቶኝ ፍቅርህን በቋንቋ ብዘምር ብዘምር ብሎኝ አሎጣ እስኪ ልሞክር ለመግለጽ ስለ አንተ ደግሜ ልበልህ አንተ እኮ ፍቅር ነህ አንተ እኮ ፍቅር ነህ (6x) አንተ እኮ ደግ ነህ (6x) አንተ እኮ ሩሩህ ነህ (6x) እንዴት አልፈዋለሁ ያልኩትን ያንን ቀን ክንድህ አሻገረኝ አለፍኩት ያንን ቀን ዛሬስ ተረዳሁኝ ቆምኩኝ እንደገና ቀና አልኩኝ ከአንገቴ ታለፈ ያ ዘመን ታለፈ ያ ዘመን (3x) ታለፈ ያ ዘመን (በኢየሱስ የማይታለፍ ምን አለ) ታለፈ ያ ዘመን (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection