Song Lyrics

ከመወለዴ ጀምሮ

Mesfin Gutu
Endihu Bewaza
ከመወለዴ ጀምሮ የማውቀው መልካም አንድ ነው ከልጅነቴ ጀምሮ የማውቀው መልካም አንድ ነው እርሱም አንተን ነው (3x) ጌታ መልካም ነው አምላኬ አምላኬ እንዳንተ ያለ ማነው (2x) ኢየሱስ ሥልጣንህ ገደብ የለው ኢየሱስ መንግሥትህ ፍጻሜ የለው በዙፋንህ ፀንተህ ጥንትም ነበርክ ዛሬም በክብር አለህ ለዘለዓለም ደግሞ በሥልጣንህ ገና ትኖራለህ ከሁሉም በላይ ነህ የኔ ጌታ፣ ሁሉን ትገዛለህ የሚወዳደርህ አቻ የለህ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ አምላኬ አምላኬ እንዳንተ … ሰምቼ ነበር በጆሮዬ ጌታ ማዳንህን ለብዙዎች ጥላ የማምለጫ አለት መሆንህን በእውነትም አዳኝ ነህ መድሃኒቴ እኔም አይቻለሁ ከዚህ ከጨለማ ከሞት መንደር በአንተ አምልጫለሁ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ጆሮዬም አልሰማም፣ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ አይኖቼም አላዩም፣ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ከቶ አልገጠመኝም፣ ለዘላለም ክበር፣ ከፍ በልልኝ(2x) እንዳንተ የሚሆን ለኔ የለም፣ አንተ ልዩ ከሁሉ በላይ ነህ፣ አልፋና ኦሜጋ የኔ ጌታ፣ ዘላለም በክብር ምትበረታ አልፋና ኦሜጋ አቻ የለህ ዘላለም በክብር ትኖራለህ ከመወለዴ ጀምሮ ….
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection