Song Lyrics

ኧረ ስንቱ

Mesfin Gutu
Endihu Bewaza
ኧረ ስንቱ በአንተ ታለፈ የእኔ ጌታ በአንተ ታለፈ (2x) እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ መስሎት ነበር ጠላቴ ደክሜ የምቀር እግዚአብሔር ግን አበረታኝ ሆነልኝ ግርማ ሞገስ ዛሬ ይኸው ዘምራለሁ ድካሜን ረስቻለሁ ሥምህን አከብራለሁ ንገሥ እልሃለሁ (2x) አልደከምኩም አልታከትኩም ጌታ ሆኖኝ ኃይሌ ዘለዓለም አመልከዋለሁ ኢየሱስ ጌታዬ በደስታ በዕልልታ በአክብሮት ደግሞም በሆታ ሥምህን አከብራልሁ ንገሥ እልሃለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection