Song Lyrics

አበቃ

Mesfin Gutu
Endihu Bewaza
አበቃ አከተመ በተባለ ጊዜ ማነው ለእኔስ ፈጥኖ የደረሰው (2x) ጌታ እኮ ነው ጌታ እኮ ነው አሃ (3x) ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገው እስራቴን ፈተህ ቀንበሬን ሰብረህ ያስጨነቀኝ ጠላት ከእግሬ ሥር ጥለህ ዛሬማ ቀና አልኩኝ ይኸው በኢየሱስ ዘለዓለም ልገዛ ልስገድልህ (2x) አምላክ እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ አባት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ሲረዳኝ በዓይኔ እያየሁ ሲያግዘኝ በዓይኔ እያየሁ (2x) ሥምህን ጠርቼ ሁሉን አለፍኩ መቼ አንተን ይዤ እኔስ አፈርኩ ዛሬም የሚያቅተኝ ሁሉ እወጣዋለሁ የአንተ ነው ኃይሉ (2x) አበቃ አከተመ በተባለ ጊዜ ማነው ለእኔስ ፈጥኖ የደረሰው (2x) ጌታ እኮ ነው ጌታ እኮ ነው አሃ (3x) ጌታ እኮ ነው ይህን ያደረገው አምላክ እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ አባት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ረዳት እንደሌለው ለምን አዝናለሁ ሲረዳኝ በዓይኔ እያየሁ ሲያግዘኝ በዓይኔ እያየሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection