የቱን ጀምሬ የቱን ልተወው ይሄ ጌታ ለእኔ ያደረገው ያደረገውን ሳስበው ሳስበው ከቁጥር በላይ ነው ለእኔ የሆነውን ሳስበው ሳስበው ከቁጥር በላይ ነው (2x) አቤት በአንተ ስንቱን አለፍኩኝ የጠላቴን ጉልበት ረገጥኩኝ ጌታ ለአንተ ምን ይሳንሃል የጠላት ምሽግ ገና ይፈርሳል ክብርህን ላውራ ዛሬም ነገም የእስራኤል ቅዱስ አንተው ተባረክ ብዙ ስራዬን አንተ ሰርተሃል አመልክህ ዘንድ ይገባኛል (2x) ከአንተ በአንተ በሆነው ነገር እዚህ ደረስኩ ሥምህ ይባረክ ደስታዬ ይኸው ፍፁም ሆነልኝ አማኑኤል ክበርልኝ የቱን ጀምሬ የቱን ልተወው ይሄ ጌታ ለእኔ ያደረገው ያደረገውን ሳስበው ሳስበው ከቁጥር በላይ ነው ለእኔ የሆነውን ሳስበው ሳስበው ከቁጥር በላይ ነው (2x)