በምስጋና ላይ ምስጋና | 3× | በዝማሬ ላይ ዝማሬ | 3× | እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለ ጩኸቴንም ሰማ ፊቱን ወደ እኔ መለሰ ከሚውጠውም ጉድጓድ ከሚይዘቅጥ ማጥ አወጣኝ እግሮቼን በአለት ላይ አቆመ አካሄዴንም አጸና እንግዲህ በህይወቴ ዘመን አመሰግንሀለሁ በአንተም ስም እጆቼን ከልቤ ጋር አነሳለሁ ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚረካ ሰው በመልካምነትህ ረክታለች በደስታም ትዘምራለች እግዚአብሔርን አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ እድል ፈንታዬ መጠጊያዬ ከለላዬ መመኪያዬ ዛሬም ለዘላለም መኖሪያዬ አንተ መልካም ነህ | 3× | ጌታ መልካም ነህ | 3× |