Song Lyrics

በብርሃንህ

የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና ነፍሳችንን አረስርሷልና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን/፬× ፩. ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ተሰቅለህ ዕዳችንን ኹሉ በደምህ ከፍለህ ሙታን ለነበርነው ሕይወትን ሰጠኸን የመንግሥት ወራሾች አደረከን አዝማች፤ የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና ጸጋ በእምነት አድኖናልና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን/፬× ፪. ብርሃንህ ጨለማውን ገፏል ብርሃንህ እንቅፋቱን ገልጧል ብርሃንህ ወደ ሕይወት መርቶናል ከጥፋት ታድጎናል በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection