1. የወደድካቸውን ሁሌም ትወዳለህ ወረት አያዉቅህም አንተ ሰው አይደለህ ሁሉም ቢለዋወጥ አንተ ያዉ አንተ ነህ አመታትህ አያልቁም አያረጅም ፍቅርህ | 4×| ርስታችን እድል ፈንታችን ሁሉም ቢቀር ከቶ ምን አጣን አንተ አለኸን ከበቂም በላይ ክበርልን በምድር በሰማይ 2. ግራ ቀኙን አየን ሁሉን ተመለከትን የኛ የመሰለን እንዳልሆነ አወቅን ከአመጣጡ ይልቅ አካሄዱ ፈጥኗል ሁሉም ግን ቢከዳን ፍቅርህ ቀርቶልናል |4×| ርስታችን መኖርያችን የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ነው | 2× | ምርኩዛችን መመኪያችን የዘላለም አምላክ እግዚአብሔር ነው| 2×|