Song Lyrics

አልፋ ኦሜጋ

አቤቱ ለቀዳሚነትህ ጥንት ለኋላኛናትህ ፍጻሜ የለህ [ 2x] አንተ እግዚአብሔር ነህ [፬X] አልፋ ኦሜጋ ፊተኛ ኋለኛ [፬X] ጌታ ዘመናትህ ዓማታትህ ቢቆጠሩ አያልቁም ለአንተ ምን ቢበዙ የዕድሜ ገደብ ከቶ አይችሉም ሊሰጡህ ዘመናትን አሳልፈህ አሳልፈህ አንተ ብቻ ትኖራለህ ትኖራለህ ዘላለማዊ ነህ ዘላለማዊ ነህ [፬X] አናልፍም ያሉ አለፉ አንሞትም ያሉትም ሞቱ ኃያላን ለአንተ ሰገዱ ኃይል የእግዚአብሔር ነው አሉ የአንተአልፋ የአንተ ኦሜጋ ሁሌ ጽኑ ነው መሽቶ ሲነጋ መንግስትህ ቋሚ ዘላለማዊ ሁሉ ሲያከትም አንተ ነህ ነዋሪ ዘላለማዊ ነህ ዘላለማዊ ነህ [፬X] ጌታ እግዚአብሔር ሆይ አንተ ያልነበርክበት ጊዜ ለቅጽበት አልነበረም አይኖርም ስልጣንህ መንግስትህ ነው ከዘላለም [፬x]
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection